ለመዘምራን አለቃ ስለ ምሥጢር የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው 2ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ ተራራዎችም ወደባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም 3ውሃዎቻቸው ጮኹ ተናወጡም ተራራዎችም ከኀይሉ የተነሣ ተናወጡ 4የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሠኛሉ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ 5እግዚአብሔር በመካከሏ ነው አትናወጥም እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል 6አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተመለሱ ርሱ ቃሉን ሰጠ ምድርም ተንቀጠቀጠች 7የሰራዊት ጌታ ከእኛ ጋራ ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው 8የእግዚአብሔርን ሥራ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ 9እስከምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነት ይሽራል ቀስትን ይሰብራል ጦርንም ይቈርጣል በእሳትም ጋሻን ያቃጥ ላል 10ዕረፉ እኔም አምላክ እንደ ኾንኹ ዕወቁ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለኹ በምድርም ላይ ከፍ ከ ፍ እላለኹ 11የሰራዊት ጌታ ከእኛ ጋራ ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው