ለመዘምራን አለቃ በመለከቶች የቆሬ ልጆች ትምህርት የፍቅር መዝሙር።
1ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለኹ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው 2ውበትኽ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል ሞገስ በከንፈሮችኽ ፈሰሰ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባረ ከኽ 3ኀያል ሆይ በቍንዥናኽና በውበትኽ ሰይፍኽን በወገብኽ ታጠቅ 4ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና ተከናወን ንገሥም ቀኝኽም በክብር ይመራኻል 5ኀያል ሆይ ፍላጻዎችኽ የተሳሉ ናቸው እነርሱም በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ አሕዛብም በበታ ችኽ ይወድቃሉ 6አምላክ ሆይ ዙፋንኽ ለዘለዓለም ነው የመንግሥትኽ በትር የቅንነት በትር ነው 7ጽድቅን ወደድኽ ዐመፃንም ጠላኽ ስለዚህ ከባልንጀራዎችኽ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይት ን ቀባኽ 8በልብሶችኽ ዅሉ ከርቤና ሽቱ ዝባድም አሉ ከዝኆን ጥርሶች አዳራሽ ደስ ያሠኙኻል 9የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርኽ ናቸው በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝኽ ትቆማለ ች 10ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ዦሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት ርሺ 11ንጉሥ ውበትሽን ወዷ፟ልና ርሱ ጌታሽ ነውና 12የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል የምድር ባለጠጋዎች አሕዛብ በፊትኽ ይማለላ ሉ 13ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ዅሉ ክብሯ ነው ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው 14በዃላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ ባልንጀራዎቿንም ወዳንተ ያቀርባሉ 15በደስታና በሐሴት ይወስዷቸዋል ወደንጉሥ ዕልፍኝም ያስገቧቸዋል 16በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ በምድርም ዅሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ 17ለልጅ ልጅ ዅሉ ስምሽን ያሳስባሉ ስለዚህ ለዓለምና ለዘለዓለም አሕዛብ ይገዙልኻል