የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ፍረድልኝ ከጽድቅ ከራቁ ሕዝብም ክርክሬን ተከራከር ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ 2አንተ አምላኬ ኀይሌም ለምን ትተወኛለኽ ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን ዐዝኜ እመላለሳለኹ 3ብርሃንኽንና እውነትኽን ላክ እነርሱ ይምሩኝ ወደቅድስናኽ ተራራና ወደ ማደሪያኽ ይውሰዱኝ 4ወደእግዚአብሔር መሠዊያ ጕልማሳነቴንም ደስ ወዳሠኛት ወደ አምላኬ እገባለኹ አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንኻለኹ 5ነፍሴ ሆይ ለምን ታዝኛለሽ ለምንስ ታውኪኛለሽ የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግ ዚአብሔር ታመኚ