ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1ቈይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናኹት ርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኸቴንም ሰማኝ 2ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው አረማመዴንም አጸና 3ዐዲስ ዝማሬን ለአምላካችን ምስጋና በአፌ ጨመረ ብዙዎች ያያሉ ይፈሩማል በእግዚአብሔርም ይታመናሉ 4እግዚአብሔርን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ምስጉን ነው 5አቤቱ አምላኬ ያደረግኸው ተኣምራት ብዙ ነው ዐሳብኽንም ምንም የሚመስለው የለም ባወራም ብናገርም ከቍጥር ዅሉ በዛ 6መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድኽም ሥጋን አዘጋጀኽልኝ የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መ ሥዋዕት አልሻኽም 7በዚያን ጊዜ አልኹ፦እንሆ መጣኹ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፏል 8አምላኬ ሆይ ፈቃድኽን ለማድረግ ወደድኹ ሕግኽም በልቤ ውስጥ ነው 9በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራኹ እንሆ ከንፈሮቼን አልከለክልም አቤቱ አንተ ጽድቄን ታውቃለኽ 10እውነትኽንም በልቤ ውስጥ አልሰወርኹም ማዳንኽንም ተናገርኹ ምሕረትኽንና እውነትኽን ከታላቅ ጉባ ኤ አልሰወርኹም 11አቤቱ አንተ ምሕረትኽን ከእኔ አታርቅ ቸርነትኽና እውነትኽ ዘወትር ይጠብቁኝ 12ቍጥር የሌላት ክፋት አግኝታኛለችና ኀጢአቶቼ ያዙኝ ማየትም ተስኖኛል ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ ል ቤም ተወኝ 13አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን 14ነፍሴን ለማጥፋት የሚወዱ ይፈሩ በአንድነትም ይጐስቍሉ በእኔ ላይ ክፋትን ሊያደርጉ የሚወዱ ወደ ዃላቸው ይመለሱ ይጐስቍሉም 15ዕሠይ ዕሠይ የሚሉኝ ዕፍረታቸውን ወዲያው ይከፈሉ 16አቤቱ የሚፈልጉኽ ዅሉ ባንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ ዅልጊዜ ማዳንኽን የሚወዱ ዘወትር እ ግዚአብሔር ታላቅ ይኹን ይበሉ 17እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ ጌታ ግን ያስብልኛል አንተ ረዳቴና መድኀኒቴ ነኽ አምላኬ ሆይ አትዘ ግይ