ለመዘምራን አለቃ ለኤዶታም የዳዊት መዝሙር።
1በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለኹ ኀጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖ ራለኹ አልኹ 2ከዝምታ የተነሣ እንደ ዲዳ ኾንኹ ለበጎ እንኳ ዝም አልኹ ቍስሌም ታደሰብኝ 3ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ ከማሰቤም የተነሣ እሳት ነደደ በአንደበቴም ተናገርኹ 4አቤቱ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያኽል እንደ ኾኑ እኔ ምን ያኽል ወደ ዃላ እንደ ምቀር ዐውቅ ዘንድ 5እንሆ ዘመኖቼን አስረጀኻቸው አካሌም በፊትኽ እንደ ኢምንት ነው ሕያው የኾነ ሰው ዅሉ በእውነት ከንቱ ብቻ ነው 6በከንቱ ይታወካል እንጂ በእውነት ሰው እንደ ጣላ ይመላለሳል ያከማቻል የሚሰበስብለትንም አያውቅም 7አኹንስ ተስፋዬ ማን ነው እግዚአብሔር አይደለምን ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው 8ከኀጢአቴ ዅሉ አድነኝ ለሰነፎችም ስድብ አታድርገኝ 9አንተ ሠርተኸኛልና ዝም አልኹ አፌንም አልከፈትኹም 10መቅሠፍትኽን ከእኔ አርቅ ከእጅኽ ብርታት የተነሣ አልቄያለኹና 11በተግሣጽኽ ስለ ኀጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው ነፍሱም እንደ ሸረሪት ድር ታልቃለች በእውነት ሰው ዅሉ ከንቱ ነው 12አቤቱ ጸሎቴን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና እንደ አባቶችም እንግዳ ነኝና 13ወደማልመለስበት ሳልኼድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ