የዳዊት መዝሙር።
1በክፉዎች ላይ አትቅና ዐመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና 2እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና 3በእግዚአብሔር ታመን መልካምንም አድርግ በምድርም ተቀመጥ ታምነኽም ተሰማራ 4በእግዚአብሔር ደስ ይበልኽ የልብኽንም መሻት ይሰጥኻል 5መንገድኽን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ በርሱም ታመን ርሱም ያደርግልኻል 6ጽድቅኽን እንደ ብርሃን ፍርድኽንም እንደ ቀትር ያመጣል 7ለእግዚአብሔር ተገዛ ተስፋም አድርገው መንገድም በቀናችለትና ጥመትን በሚያደርግ ሰው አትቅና 8ከቍጣ ራቅ መዓትንም ተው እንዳትበድል አትቅና 9ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ 10ገና ጥቂት ኀጢአተኛም አይኖርም ትፈልገዋለኽ ቦታውንም አታገኝም 11ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል 12ኀጢአተኛ ጻድቁን ይመለካከተዋል ጥርሱንም በርሱ ላይ ያንገጫግጫል 13እግዚአብሔር ይሥቅበታል ቀኑ እንደሚደርስ አይቷልና 14ኀጢአተኛዎች ሰይፋቸውን መዘዙ ቀስታቸውንም ገተሩ ድኻውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ ልበ ቅኖችን ም ይወጉ ዘንድ 15ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ ቀስታቸውም ይሰበር 16ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከኀጢአተኛዎች ሀብት ይበልጣል 17የኃጥኣን ክንድ ትሰበራለችና እግዚአብሔር ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል 18የንጹሓንን መንገድ እግዚአብሔር ያውቃል ርስታቸውም ለዘለዓለም ነው 19በክፉ ዘመንም አያፍሩም በራብ ዘመንም ይጠግባሉ 20ኃጥኣን ግን ይጠፋሉ የእግዚአብሔር ጠላቶች በከበሩና ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ እንደ ጢስ ይጠፋሉ 21ኀጢአተኛ ይበደራል አይከፍልምም ጻድቅ ግን ይራራል ይሰጣልም 22ርሱን የሚባርኩት ምድርን ይወርሳሉና የሚረግሙት ግን ይጠፋሉ 23የሰው አካኼድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል መንገዱንም ይወዳ፟ል 24ቢወድቅም ለድንጋፄ አይጣልም እግዚአብሔር እጁን ይዞ ይደግፈዋልና 25ጐለመስኹ አረጀኹም ጻድቅ ሲጣል ዘሩም እኽል ሲለምን አላየኹም 26ዅልጊዜ ይራራል ያበድርማል ዘሩም በበረከት ይኖራል 27ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ ለዘለዓለምም ትኖራለኽ 28እግዚአብሔር ፍርዱን ይወዳ፟ልና ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል የኃጥኣን ዘር ግን ይጠፋል 29ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ በርሷም ለዘለዓለም ይኖራሉ 30የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል አንደበቱም ፍርድን ይናገራል 31የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው በርምጃውም አይሰናከልም 32ኀጢአተኛ ጻድቁን ይመለከተዋል ሊገድለውም ይወዳ፟ል 33እግዚአብሔር ግን በእጁ አይተወውም በተፋረደውም ጊዜ አያሸንፈውም 34እግዚአብሔርን ደጅ ጥና መንገዱንም ጠብቅ ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግኻል ኀጢአተኛ ዎችም ሲጠፉ ታያለኽ 35ኃጥኣን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየኹት 36ብመለስ ግን ዐጣኹት ፈለግኹት ቦታውንም አላገኘኹም 37ቅንነትን ጠብቅ ጽድቅንም እይ ለሰላም ሰው ቅሬታ አለውና 38በደለኛዎች በአንድነት ይጠፋሉ የኀጢአተኛዎች ቅሬታ ይጠፋል 39የጻድቃን መድኀኒታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው ርሱ ነው 40እግዚአብሔር ይረዳቸዋል ያድናቸዋልም ከኀጢአተኛዎችም እጅ ያወጣቸዋል ያድናቸዋል በርሱ ታምነዋል ና