የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ የሚበድሉኝን በድላቸው የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው 2ጥሩርና ጋሻ ያዝ እኔንም ለመርዳት ተነሥ 3ሰይፍኽን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦መድኀኒትሽ እኔ ነኝ በላት 4ነፍሴን የሚሹ ዅሉ ይፈሩ ይጐስቈሉም ክፋትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይፈሩ ወደ ዃላቸውም ይበሉ 5በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይኹኑ የእግዚአብሔርም መልአክ ያስጨንቃቸው 6መንገዳቸው ድጥና ጨለማ ይኹን የእግዚአብሔርም መልአክ ያሳ፟ዳ፟ቸው 7በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛልና ነፍሴን በከንቱ አበሳጭተዋልና 8ያላወቁት ወጥመድ ይምጣባቸው የሸሸጉትም ወጥመድ ይያዛቸው በዚህ ወጥመድ ውስጥ ይውደቁ 9ነፍሴ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይላታል በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች 10ዐጥንቶቼ ዅሉ እንዲህ ይሉኻል፦አቤቱ እንደ አንተ ማን ነው ችግረኛን ከሚቀማው እጅ ችግረኛንና ድኻውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለኽ 11የክፋት ምስክሮች ተነሡብኝ የማላውቀውንም በእኔ ላይ ተናገሩ 12ስለ በጎ ክፋትን መለሱልኝ ነፍሴንም ልጆችን አሳጧት 13እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኹ ነፍሴንም በጾም አደከምዃት ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ 14ለወዳጄና ለወንድሜ እንደማደርግ አደረግኹ ለእናቱም እንደሚያለቅስ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግኹ 15በእኔ ላይ ተሰበሰቡ ደስም አላቸው ግፈኛዎች በእኔ ላይ ተሰበሰቡ እኔም አላውቅኹም ቀደዱኝ አል ተዉኝምም 16ፈተኑኝ በሣቅም ዘበቱብኝ ጥርሳቸውንም በእኔ ላይ አንቀጫቅጩ 17አቤቱ እስከ መቼ ድረስ ታይልኛለኽ ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው ብችነቴንም ከአንበሳዎች አድናት 18አቤቱ በታላቁ ጉባኤ ውስጥ እገዛልኻለኹ በብዙ ሕዝብ መካከልም አመሰግንኻለኹ 19በግፍ የሚጠሉኝ በላዬ ደስ አይበላቸው በከንቱ የሚጣሉኝም በዐይናቸው አይጣቀሱብኝ 20ለኔስ ሰላምን ይናገሩኛልና በቍጣም ሽንገላን ይመክራሉ 21አፋቸውንም በእኔ ላይ አላቀቁ ዕሠይ ዕሠይ ዐይናችን አየው ይላሉ 22አቤቱ አንተ አየኸው ዝም አትበል አቤቱ ከእኔ አትራቅ 23አምላኬ ጌታዬም ወደ ፍርዴ ተነሥ አቤቱ ፍርዴን አድምጥ 24አቤቱ አምላኬ እንደ ጽድቅኽ ፍረድልኝ በላዬም ደስ አይበላቸው 25በልባቸው፦ዕሠይ ዕሠይ ነፍሳችንን ደስ አላት አይበሉ ደግሞም፦ዋጥነው አይበሉ 26በመከራዬ ደስ የሚላቸው ይፈሩ በአንድነትም ይጐስቍሉ በእኔ ላይ የሚታበዩ ዕፍረትንና ጕስቍልናን ይልበሱ 27ጽድቄን የሚወዷ፟ት ደስ ይበላቸው ሐሴትንም ያድርጉ የባሪያውን ሰላም የሚወድ፟ እግዚአብሔር ታላ ቅ ይኹን ዘወትር ይበሉ 28ምላሴ ጽድቅኽን ዅልጊዜም ምስጋናኽን ይናገራል