የዳዊት መዝሙር።
1ጻድቃን ሆይ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችኹ ለቅኖች ምስጋና ይገ፟ባ፟ል 2እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት ዐሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት 3ዐዲስ ቅኔም ተቀኙለት በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ 4የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ዅሉ በእምነት ነውና 5ጽድቅንና ፍርድን ይወዳ፟ል የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች 6በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሰራዊታቸውም ዅሉ በአፉ እስትንፋስ 7የባሕርን ውሃ እንደ ረዋት የሚሰበስበው ቀላዮችንም በመዝገቦች የሚያኖራቸው 8ምድር ዅሉ እግዚአብሔርን ትፍራው በዓለም የሚኖሩ ዅሉም ከርሱ የተነሣ ይደንግጡ 9ርሱ ተናግሯልና ኾኑም ርሱ አዘዘ ጸኑም 10እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ያጠፋል የአሕዛብንም ዐሳብ ይመልሳል 11የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል የልቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው 12እግዚአብሔር አምላኩ የሚኾንለት ሕዝብ ምስጉን ነው ርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ 13እግዚአብሔር ከሰማይ ተመለከተ የሰውንም ልጆች ዅሉ አየ 14ከማደሪያው ቦታ ኾኖ በምድር ወደሚኖሩ ዅሉ ተመለከተ 15ርሱ ብቻውን ልባቸውን የሠራ ሥራቸውንም ዅሉ የሚያስተውል 16ንጉሥ በሰራዊቱ ብዛት አይድንም ኀያልም በኀይሉ ብዛት አያመልጥም 17ፈረስም ከንቱ ነው አያድንም በኀይሉም ብዛት አያመልጥም 18እንሆ የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደሚፈሩት ናቸው በምሕረቱም ወደሚታመኑ 19ነፍሳቸውን ከሞት ያድን ዘንድ በራብም ጊዜ ይመግባቸው ዘንድ 20ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች ረዳታችንና መጠጊያችን ርሱ ነውና 21ልባችን በርሱ ደስ ይለዋልና በቅዱስ ስሙም ታምነናልና 22አቤቱ ምሕረትኽ በላያችን ትኹን ባንተ እንደ ታመን፟