የዳዊት ትምህርት መዝሙር።
1መተላለፉ የቀረችለት ኀጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው 2እግዚአብሔር በደልን የማይቈጥርበት በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው ምስጉን ነው 3ዅልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ ዝም ባልኹ ጊዜ ዐጥንቶቼ ተበላሹ 4በቀንና በሌሊት እጅኽ ከብዳብኛለችና ርጥበቴም ለበጋ ትኵሳት ተለወጠ 5ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅኹ በደሌንም አልሸፈንኹም ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለኹ አልኹ አ ንተም የልቤን ኀጢአት ተውኽልኝ 6ስለዚህ ቅዱስ ዅሉ በምቹ ጊዜ ወዳንተ ይለምናል ብዙ የጥፋት ውሃም ወደ ርሱ አይቀርብም 7አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነኽ ከጣርም ትጠብቀኛለኽ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነኽ 8አስተምርኻለኹ በምትኼድበትም መንገድ እመራኻለኹ ዐይኖቼን ባንተ ላይ አጠናለኹ 9ወዳንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጕንጫቸውን እንደሚለጕሟቸው ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትኹኑ 10በኀጢአተኛ ብዙ መቅሠፍት አለበት በእግዚአብሔር የሚታመነውን ግን ምሕረት ይከበ፟ዋል 11ጻድቃን ሆይ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችኹ ሐሤትም አድርጉ ልባችኹም የቀና ዅላችኹ እልል በሉ