ከድንኳን በመውጣት ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1የአምላክ ልጆች ሆይ ለእግዚአብሔር አምጡ ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ 2የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ 3የእግዚአብሔር ድምፅ በውሃዎች ላይ የክብር አምላክ አንጐደጐደ እግዚአብሔር በብዙ ውሃዎች ላይ 4የእግዚአብሔር ድምፅ በኀይል ነው የእግዚአብሔር ድምፅ በታላቅ ክብር ነው 5የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል 6እንደ ጥጃ ሊባኖስን አንድ ቀን እንዳለው አውሬ ልጅ ስርዮንን ያዘልላቸዋል 7የእግዚአብሔር ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል 8የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል 9የእግዚአብሔር ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል ጫካዎቹንም ይገልጣል ዅሉም በመቅደሱ፦ምስጋና ይላል 10እግዚአብሔር የጥፋት ውሃን ሰብስቧል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ኾኖ ይቀመጣል 11እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይልን ይሰጣል እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል