የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ወዳንተ እጠራለኹ ዝም ብትለኝ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልመስል አንተ አምላኬ ዝም አትበለኝ 2ወደ መቅደስኽ ማደሪያ እጄን ባነሣኹ ጊዜ ወዳንተ የጮኽኹትን የልመናዬን ቃል ስማ 3ከኃጥኣንና ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ነፍሴን አትውሰዳት ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋራ ሰላም ከሚናገሩት ጋራ አትጣለኝ 4እንደ ሥራቸው እንደ አካኼዳቸውም ክፋት ስጣቸው እንደ እጃቸውም ሥራ ስጣቸው ፍዳቸውን ወደ ራሳቸ ው መልስ 5ወደእግዚአብሔር ሥራ ወደ እጆቹም አደራረግ አላሰቡምና ያፈርሳቸዋል እንጂ አይሠራቸውም 6የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና እግዚአብሔር ይመስገን 7እግዚአብሔር ኀይሌና ጋሻዬ ነው ልቤ በርሱ ታመነ እኔም ተረዳኹ ሥጋዬም ደስ ይለዋል ፈቅጄም አመ ሰግነዋለኹ 8እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይላቸው ነው ለቀባውም የመድኀኒቱ መታመኛ ነው 9ሕዝብኽን አድን ርስትኽንም ባርክ ጠብቃቸው ለዘለዓለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው