ሳይቀባ፥ የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኀኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው 2ክፉዎች አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ 3ሰራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለኹ 4እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንኹት ርሷንም እሻለኹ በሕይወቴ ዘመን ዅሉ በእግዚአብሔር ቤት እ ኖር ዘንድ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኘውንም አይ ዘንድ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ 5በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና በአለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎ ኛልና 6እንሆ አኹን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋኹ ለእግዚአብሔር እቀኛለኹ እዘምርለትማለኹ 7አቤቱ ወዳንተ የጮኽኹትን ቃሌን ስማኝ ማረኝና አድምጠኝ 8አንተ ፊቴን ሹት ባልኽ ጊዜ፦አቤቱ ፊትኽን እሻለኹ ልቤ አንተን አለ 9ፊትኽን ከእኔ አትሰውር ተቈጥተኽ ከባሪያኽ ፈቀቅ አትበል ረዳት ኹነኝ አትጣለኝም የመድኀኒቴም አ ምላክ ሆይ አትተወኝ 10አባቴና እናቴ ትተውኛልና እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ 11አቤቱ መንገድኽን አስተምረኝ ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ 12የሐሰት ምስክሮችና ዐመፀኛዎች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፈቃድ አትስጠኝ 13የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለኹ 14እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብኽም ይጽና እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ