የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ወዳንተ ነፍሴን አነሣለኹ 2አምላኬ አንተን ታመንኹ አልፈር ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ 3አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ 4አቤቱ መንገድኽን አመልክተኝ ፍለጋኽንም አስተምረኝ 5አንተ የመድኀኒቴ አምላክ ነኽና በእውነትኽ ምራኝ አስተምረኝም ቀኑን ዅሉ አንተን ተስፋ አድርጌያ ለኹ 6አቤቱ ምሕረትኽንና ቸርነትኽን ዐስብ ከጥንት ዠምሮ ናቸውና 7የልጅነቴን ኀጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ አቤቱ ስለቸርነትኽ ብዛት እንደ ምሕረትኽ ዐስበኝ 8እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው ስለዚህ ኀጢአተኛዎችን በመንገድ ይመራቸዋል 9ገሮችን በፍርድ ይመራል ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል 10የእግዚአብሔር መንገድ ዅሉ ቸርነትና እውነት ነው ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ 11አቤቱ ኀጢአቴ እጅግ ነውና ስለ ስምኽ ይቅር በለኝ 12እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል 13ነፍሱ በመልካም ታድራለች ዘሩም ምድርን ይወርሳል 14እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኀይላቸው ነው ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል 15ርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዐይኖቼ ዅልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው 16እኔ ብቻዬንና ችግረኛ ነኝና ፊትኽን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም 17የልቤ ችግር ብዙ ነው ከጭንቀቴ አውጣኝ 18ድካሜንና መከራዬን እይ ኀጢአቴንም ዅሉ ይቅር በለኝ 19ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ የግፍም ጥል ጠልተውኛል 20ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ አንተን ታምኛለኹና አልፈር 21አንተን ተስፋ አድርጌያለኹና የውሀትና ቅንነት ይጠብቁኝ 22አቤቱ እስራኤልን ከመከራው ዅሉ አድነው