በመጀመሪያ ሰንበት የዳዊት መዝሙር።
1ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት ዓለምም በርሷም የሚኖሩ ዅሉ 2ርሱ በባሕሮች መሥርቷታልና በፈሳሾችም አጽንቷታልና 3ወደእግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል 4እጆቹ የነጹ ልቡም ንጹሕ የኾነ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ 5ርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኀኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል 6ይህች ትውልድ ርሱን የምትፈልግ ናት የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ 7እናንት መኳንንቶች በሮችን ክፈቱ የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ የክብርም ንጉሥ ይግባ 8ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኀያል እግዚአብሔር ነው በሰልፍ ኀያል 9እናንተ መኳንንቶች በሮችን ክፈቱ የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ የክብርም ንጉሥ ይግባ 10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው የጭፍራዎች አምላክ እግዚአብሔር ርሱ የክብር ንጉሥ ነው