የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም 2በለመለመ መስክ ያሳድረኛል በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል 3ነፍሴን መለሳት ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ 4በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብኼድ አንተ ከእኔ ጋራ ነኽና ክፉን አልፈራም በትርኽና ምርኵዝኽ እነር ሱ ያጸናኑኛል 5በፊቴ ገበታን አዘጋጀኽልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባኽ ጽዋዬም የተረፈ ነው 6ቸርነትኽና ምሕረትኽ በሕይወቴ ዘመን ዅሉ ይከተሉኛል በእግዚአብሔርም ቤት ለዘለዓለም እኖራለኹ