ለመዘምራን አለቃ ስለ ንጋት ኀይል የዳዊት መዝሙር።
1አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነኽ 2አምላኬ በቀን ወዳንተ እጠራለኹ አልመለስኽልኝም በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም 3በእስራኤል የተመሰገንኽ አንተ ግን በቅድስና ትኖራለኽ 4አባቶቻችን አንተን ተማመኑ ተማመኑ አንተም አዳንኻቸው 5ወዳንተ ጮኹ አመለጡም አንተንም ተማመኑ አላፈሩም 6እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለኹም የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅኹ ነኝ 7የሚያዩኝ ዅሉ ይላገዱብኛል ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይላሉ 8በእግዚአብሔር ተማመነ ርሱንም ያድነው ቢወደ፟ውስ ያድነው 9አንተ ግን ከሆድ አውጥተኸኛልና በእናቴ ጡት ሳለኹም ባንተ ታመንኹ 10ከማሕፀን ዠምሮ ባንተ ላይ ተጣልኹ ከእናቴ ሆድ ዠምረኽ አንተ አምላኬ ነኽ 11ጭንቀት ቀርባለችና የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ 12ብዙ በሬዎች ከበቡኝ የሰቡትም ፍሪዳዎች ያዙኝ 13እንደ ነጣቂና እንደሚጮኽ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ 14እንደ ውሃ ፈሰስኹ ዐጥንቶቼም ዅሉ ተለያዩ ልቤ እንደ ሠም ኾነ በአንዠቴም መካከል ቀለጠ 15ኀይሌ እንደ ገል ደረቀ በጕረሮዬም ምላሴ ተጣጋ ወደሞትም አሸዋ አወረድኸኝ 16ብዙ ውሻዎች ከበ፟ውኛልና የክፋተኛዎች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ 17ዐጥንቶቼ ዅሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም 18ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ 19አንተ ግን አቤቱ ከእኔ አትራቅ አንተ ጕልበቴ እኔን ለመርዳት ፍጠን 20ነፍሴን ከሰይፍ አድናት ብቻነቴንም ከውሻዎች እጅ 21ከአንበሳ አፍ አድነኝ ብቻነቴንም አንድ ቀንድ ካላቸው 22ስምኽን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለኹ በጉባኤም መካከል አመሰግንኻለኹ 23እግዚአብሔርን የምትፈሩ አመስግኑት የያዕቆብ ዘር ዅላችኹ አክብሩት የእስራኤልም ዘር ዅላችኹ ፍ ሩት 24የችግረኛን ችግር አልናቀምና ቸልም አላለምና ፊቱንም ከእኔ አልሰወረምና ነገር ግን ወደ ርሱ በ ጮኽኹ ጊዜ ሰማኝ 25በታላቅ ጉባኤ ምስጋናዬ ከአንተ ዘንድ ነው ርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እሰጣለኹ 26ችግረኛዎች ይበላሉ ይጠግቡማል እግዚአብሔርንም የሚሹት ያመሰግኑታል ልባቸውም ለዘለዓለም ሕያው ይኾናል 27የምድር ዳርቻዎች ዅሉ ያስቡ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሱ የአሕዛብ ነገዶች ዅሉ በፊቱ ይሰግዳሉ 28መንግሥት ለእግዚአብሔር ነውና ርሱም አሕዛብን ይገዛል 29የምድር ደንዳናዎች ዅሉ ይበላሉ ይሰግዳሉም ወደ መሬት የሚወርዱት ዅሉ በፊቱ ይንበረከካሉ ነፍሴ ም ስለ ርሱ በሕይወት ትኖራለች 30ዘሬ ይገዛለታል የምትመጣው ትውልድ ለእግዚአብሔር ትነግረዋለች 31ጽድቁንም ለሚወለደው ሕዝብ እግዚአብሔር ያደረገውን ጽድቁን ይነግራሉ