ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ በኀይልኽ ንጉሥ ደስ ይለዋል በማዳንኽ እጅግ ሐሤትን ያደርጋል 2የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም 3በበጎ በረከት ደርሰኽለታልና ከክቡር ዕንቍ የኾነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርኽ 4ሕይወትን ለመነኽ ሰጠኸውም ለረዥም ዘመን ለዘለዓለሙ 5በማዳንኽ ክብሩ ታላቅ ነው ክብርንና ምስጋናን ጨመርኽለት 6የዘለዓለም በረከትን ሰጥተኸዋልና በፊትኽም ደስታ ደስ ታሠኘዋለኽ 7ንጉሥ በእግዚአብሔር ተማምኗልና በልዑልም ምሕረት አይናወጥም 8እጅኽ ጠላቶችኽን ዅሉ ታግኛቸው ቀኝኽም የሚጠሉኽን ዅሉ ታግኛቸው 9በተቈጣኽም ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው እግዚአብሔር በቍጣው ያጠፋቸዋል እሳትም ትበላቸዋለ ች 10ፍሬያቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለኽ 11ክፋትን ባንተ ላይ ዘርግተዋልና የማይቻላቸውንም ምክር ዐሰቡ 12ወደ ዃላቸው ትመልሳቸዋለኽ ፍላጻን በፊታቸው ላይ ታዘጋጃለኽ 13አቤቱ በኀይልኽ ከፍ ከፍ በል ጽናትኽንም እናመሰግናለን እንዘምርማለን