ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማኽ የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምኽ 2ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልኽ ከጽዮንም ያጥናኽ 3ቍርባንኽን ዅሉ ያስብልኽ የሚቃጠል መሥዋዕትኽን ያለምልምልኽ 4እንደ ልብኽ ይስጥኽ ፈቃድኽንም ዅሉ ይፈጽምልኽ 5በማዳንኽ ደስ ይለናል በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን ልመናኽን ዅሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልኽ 6እግዚአብሔር የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ ዐወቅኹ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል በቀኙ ብርታት ማዳን 7እነዚያ በሠረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን 8እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ እኛ ግን ተነሣን ጸንተንም ቆምን 9አቤቱ ንጉሥን አድነው በጠራንኽም ቀን ስማን