የሐጌና የዘካርያስ መዝሙር።
1ሃሌ ሉያ እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት በአርያም አመስግኑት 2መላእክቱ ዅሉ አመስግኑት ሰራዊቱ ዅሉ አመስግኑት 3ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት ከዋክብትና ብርሃን ዅሉ አመስግኑት 4ሰማየ ሰማያት አመስግኑት የሰማያት በላይም ውሃ 5ርሱ ብሏልና ኾኑም ርሱም አዟ፟ልና ተፈጠሩም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት 6ለዘለዓለም ዓለም አቆማቸው ትእዛዝን ሰጠ አያልፉምም 7እባቦች ጥልቆችም ዅሉ እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት 8እሳትና በረዶ ዐመዳይና ውርጭ ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም 9ተራራዎች ኰረብታዎችም ዅሉ የሚያፈራም ዛፍ ዝግባም ዅሉ 10አራዊትም እንስሳትም ዅሉ ተንቀሳቃሾችም የሚበሩ፟ ወፎችም 11የምድር ነገሥታት አሕዛብም ዅሉ አለቃዎች የምድርም ፈራጆች ዅሉ 12ጕልማሳዎችና ቈነዣዥቶች ሽማግሌዎችና ልጆች 13የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና ምስጋናውም በሰማይና በምድር ላይ ነው 14የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል የቅዱሳኑንም ዅሉ ምስጋና ወደ ርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ልጆ ች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል ሃሌ ሉያ