የሐጌና የዘካርያስ መዝሙር።
1(12) ኢየሩሳሌም ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ 2(13) ጽዮንም ሆይ ለአምላክሽ እልል በዪ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና ልጆችንም በውስጥሽ ባርኳልና 3(14) በወሰንሽም ሰላምን አደረገ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ 4(15) ነገሩን ወደ ምድር ይሰዳ፟ል ቃሉም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል 5(16) ዐመዳዩን እንደ ባዘቶ ይሰጣል ጉሙን እንደ ዐመድ ይበትነዋል 6(17) በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል በበረዶውስ ፊት ማን ይቆማል 7(18) ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል ነፋሱን ያነፍሳል ውሃዎችንም ያፈሳ፟ል 8(19) ቃሉን ለያዕቆብ ሥርዐቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይናገራል 9(20) ለሌላዎች አሕዛብ ዅሉ እንዲህ አላደረገም ፍርዱንም አልገለጠላቸውም ሃሌ ሉያ