ሃሌ ሉያ።
1ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር ዐዲሱን ቅኔ ተቀኙለት ምስጋናው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው 2እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ 3ስሙን በዘፈን ያመስግኑ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት 4እግዚአብሔር በሕዝቡ ተደስቷልና የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና 5ቅዱሳን በክብር ይመካሉ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ 6የእግዚአብሔር ምስጋና በጕረሯቸው ነው ኹለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጃቸው ነው 7በአሕዛብ ላይ በቀልን በሰዎችም መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ 8ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት አለቃዎቻቸውንም በእግር ብረት ያስሩ ዘንድ 9የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ ለቅዱሳን ዅሉ ይህች ክብር ናት ሃሌ ሉያ