የሐጌና የዘካርያስ መዝሙር።
1ሃሌ ሉያ ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ 2በሕይወቴ እግዚአብሔርን አመሰግናለኹ በምኖርበት ዘመን ዅሉ ለአምላኬ እዘምራለኹ 3ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቃዎች አትታመኑ 4ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል ያን ጊዜ ምክሩ ዅሉ ይጠፋል 5የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የኾነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የኾነ ሰው ምስጉን ነው 6ርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱ ያለውንም ዅሉ የፈጠረ እውነትን ለዘለዓለም የሚጠብቅ 7ለተበደሉት የሚፈርድ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው እግዚአብሔር የታሰሩትን ይፈታል 8እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣል እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኛዎች ያደርጋቸዋል እግዚአብሔር ጻድቃ ንን ይወዳ፟ል 9እግዚአብሔር ስደተኛዎችን ይጠብቃል ድኻ አደጎችንና ባልቴቶችን ይቀበላል የኀጢአተኛዎችንም መንገድ ያጠፋል 10እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይነግሣል ጽዮን ሆይ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው ሃሌ ሉያ