ልጁ ባሳደደው ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ጸሎቴን ስማ በእውነትኽ ልመናዬን አድምጥ በጽድቅኽም መልስልኝ 2ሕያው ዅሉ በፊትኽ ጻድቅ አይደለምና ከባሪያኽ ጋራ ወደ ፍርድ አትግባ 3ጠላትኽ ነፍሴን አሳዷ፟ታል ሕይወቴንም በምድር ውስጥ አጐስቍሏታል ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል 4ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ 5የቀድሞውን ዘመን ዐሰብኹ ሥራኽንም ዅሉ አሰላሰልኹ የእጅኽንም ሥራ ተመለከትኹ 6እጆቼን ወዳንተ ዘረጋኹ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች 7አቤቱ ፈጥነኽ ስማኝ ነፍሴ አልቃለች ፊትኽን ከእኔ አትመልስ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልኹን 8አንተን ታምኛለኹና በማለዳ ምሕረትኽን አሰማኝ አቤቱ ነፍሴን ወዳንተ አንሥቻለኹና የምኼድበትን መ ንገድ አስታውቀኝ 9አቤቱ ወዳንተ ተማፅኛለኹና ከጠላቶቼ አድነኝ 10አንተ አምላኬ ነኽና ፈቃድኽን ለማድረግ አስተምረኝ ቅዱስ መንፈስኽም በጽድቅ ምድር ይምራኝ 11አቤቱ ስለ ስምኽ ሕያው አድርገኝ በጽድቅኽም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት 12በምሕረትኽ ጠላቶቼን ደምስሳቸው እኔ ባሪያኽ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቋትን ዅሉ አጥፋቸው