የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ወዳንተ ጮኽኹ ስማኝ ወዳንተ ስጮኽም የልመናዬን ቃል አድምጥ 2ጸሎቴን በፊትኽ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ እጅ መንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትኹን 3አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ 4ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው ዐመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋራ ለኀጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ ከ ምርጦቻቸውም ጋራ አልተባበር 5ጻድቅ በምሕረት ይገሥጸኝ ይዝለፈኝም የኀጢአተኛ ዘይት ግን ራሴን አይቅባ ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና 6ኀያላናቸው በአለት አጠገብ ተጣሉ ጣፋጭ ናትና ቃሌን ይሰማሉ 7በምድር ላይ እንደ ተሰነጠቀ እንደ መሬት ጓል እንዲሁ ዐጥንቶቻችን በሲኦል ተበተኑ 8አቤቱ ጌታ ዐይኖቼ ወዳንተ ናቸውና ባንተ ታመንኹ ነፍሴን አታውጣት 9ከሰወሩብኝ ወጥመድ ዐመፅንም ከሚያደርጉ ሰዎች ዕንቅፋት ጠብቀኝ 10እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ ኀጢአተኛዎች በወጥመዳቸው ይውደቁ