ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ከክፉ ሰው አድነኝ በልባቸውም ክፉ ካሰቡ ከዐመፀኛዎች ሰዎች ጠብቀኝ 2ቀኑን ዅሉ ለሰልፍ ይከማቻሉ 3ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ ከከንፈራቸው በታች የእፍኝት መርዝ ነው 4አቤቱ ከኀጢአተኛዎች እጅ ጠብቀኝ ርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ ከዐመፀኛዎች አድነኝ 5ትዕቢተኛዎች ወጥመድን ሰወሩብኝ ለእግሮቼም የወጥመድ ገመድን ዘረጉ በመንገድ ዕንቅፋትን አኖሩ 6እግዚአብሔርንም፦አንተ አምላኬ ነኽ የልመናዬን ቃል አቤቱ አድምጥ አልኹት 7አቤቱ ጌታዬ የመድኀኒቴ ጕልበት በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንኽ 8አቤቱ ከምኞቴ የተነሣ ለኀጢአተኛዎች አትስጠኝ በላዬ ተማከሩ እንዳይጓደዱ አትተወኝ 9የሚከቡ፟ኝን ራስ የከንፈራቸው ክፋት ይክደናቸው 10የእሳት ፍም በላያቸው ይውደቅ እንዳይነሡም ወደ እሳትና ወደ ማዕበል ይጣሉ 11ተናጋሪ ሰው በምድር ውስጥ አይጸናም ዐመፀኛን ሰው ክፋት ለጥፋት ይፈልገዋል 12እግዚአብሔር ለድኻ ዳኝነትን ለችግረኛም ፍርድን እንዲያደርግ ዐወቅኹ 13ጻድቃንም በእውነት ስምኽን ያመሰግናሉ ቀኖችም በፊትኽ ይኖራሉ