ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ መረመርኸኝ ዐወቅኸኝም 2አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ዐወቅኽ ዐሳቤን ዅሉ ከሩቅ አስተዋልኽ 3ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርኽ መንገዶቼን ዅሉ ቀድመኽ ዐወቅኽ 4የዐመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ 5አቤቱ አንተ እንሆ የቀድሞውንና የዃላውን ዐወቅኽ አንተ ፈጠርኸኝ እጅኽንም በላዬ አደረግኽ 6ዕውቀትኽ ከእኔ ይልቅ ተደነቀች በረታች ወደ ርሷም ለመድረስ አልችልም 7ከመንፈስኽ ወዴት እኼዳለኹ ከፊትኽስ ወዴት እሸሻለኹ 8ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለኽ ወደ ሲኦልም ብወርድ በዚያ አለኽ 9እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ እስከባሕር መጨረሻም ብበር፟ 10በዚያ እጅኽ ትመራኛለች ቀኝኽም ትይዘኛለች 11በእውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትኾናለች 12ጨለማ ባንተ ዘንድ አይጨልምምና ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃኗ ነ ው 13አቤቱ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረኻልና በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል 14ግሩምና ድንቅ ኾኜ ተፈጥሬያለኹና አመሰግንኻለኹ ሥራኽ ድንቅ ነው ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች 15እኔ በስውር በተሠራኹ ጊዜ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም 16ያልተሠራ አካሌን ዐይኖችኽ አዩኝ የተፈጠሩ ቀኖቼ ዅሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍኽ ተጻፉ 17አቤቱ ዐሳቦችኽ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ! 18ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ ተነሣኹም እኔም ገና ከአንተ ጋራ ነኝ 19አቤቱ አንተ ኀጢአተኛዎችን የምትገድል ከኾንኽስ የደም ሰዎች ሆይ ከእኔ ፈቀቅ በሉ 20በክፋት ይናገሩብኻልና ጠላቶችኽም በከንቱ ያምፁብኻል 21አቤቱ የሚጠሉኽን እኔ የጠላኹ አይደለኹምን ስለ ጠላቶችኽም አልተሰቀቅኹምን 22ፍጹም ጥል ጠላዃቸው ጠላቶችም ኾኑኝ 23አቤቱ መርምረኝ ልቤንም ዕወቅ ፍተነኝ መንገዴንም ዕወቅ 24በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ የዘለዓለምንም መንገድ ምራኝ