የዳዊት መዝሙር።
1በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን 2በአሓያ ዛፎቿ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን 3የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን የወሰዱንም፦የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን 4የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን 5ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ 6ባላስብሽ ምላሴ በጕረሮዬ ይጣበቅ ከደስታዬ ዅሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድ፟ 7አቤቱ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች ዐስብ እስከ መሠረቷ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሏትን 8አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው 9ሕፃናትሽን ይዞ በአለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው