ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 2የአማልክትን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 3የጌታዎችን ጌታ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 4ርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 5ሰማያትን በብልኀት የሠራ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 6ምድርን በውሃ ላይ ያጸና ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 7ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 8ለፀሓይ ቀንን ያስገዛው ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 9ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 10ከበኵራቸው ጋራ ግብጽን የመታ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 11እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 12በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 13ቀይ ባሕርን በየክፍሉ የከፈለ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 14እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 15ፈርዖንንና ሰራዊቱን በቀይ ባሕር የጣለ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 16ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 17ታላላቅ ነገሥታትን የመታ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 18ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 19የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 20የባሳንን ንጉሥ ዐግን ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 21ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 22ለባሪያው ለእስራኤል ርስት ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 23እኛን በመዋረዳችን ዐስቦናልና ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 24ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 25ለሥጋ ዅሉ ምግብን የሚሰጥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና 26የሰማይን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና