የመዓርግ መዝሙር።
1እስራኤል ከትንሽነቴ ዠምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ይበል 2ከትንሽነቴ ዠምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ነገር ግን አላሸነፉኝም 3ኀጢአተኛዎች በዠርባዬ ላይ መቱኝ ኀጢአታቸውንም አስረዘሟት 4እግዚአብሔር ጻድቅ ነው የኀጢአተኛዎችን ዐንገታቸውን ቈረጠ 5ጽዮንን የሚጠሉ ዅሉ ይፈሩ ወደ ዃላቸውም ይመለሱ 6በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር ሳይነቀል እንደሚደርቅ 7ለሚያጭደው እጁን ነዶዎቹን ለሚሰበስብ ዕቅፉን እንደማይሞላ ይኹኑ 8በመንገዱም የሚያልፉ፦የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይኹን በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችዃለ ን አይሉም