የመዓርግ መዝሙር።
1አቤቱ አንተን ከጥልቅ ጠራኹኽ 2አቤቱ ድምፄን ስማ ዦሮኽ የልመናዬን ቃል የሚያደምጥ ይኹን 3አቤቱ ኀጢአትንስ ብትጠባበቅ አቤቱ ማን ይቆማል 4ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና 5አቤቱ ስለ ስምኽ ተስፋ አደረግኹኽ ነፍሴ በሕግኽ ታገሠች 6ከማለዳው ሰዓት ዠምሮ እስከ ሌሊት ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች 7ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት በርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን ነውና እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመን 8ርሱም እስራኤልን ከኀጢአቱ ዅሉ ያድነዋል