የመዓርግ መዝሙር።
1እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኛዎች በከንቱ ይደክማሉ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከ ንቱ ይተጋል 2በማለዳ መገሥገሣችኹም ከንቱ ነው ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ እናንተ የመከራን እንጀራ የምት በሉ ከተቀመጣችኹበት ተነሡ 3እንሆ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው የሆድም ፍሬ የርሱ ዋጋ ነው 4በኀያል እጅ እንዳሉ ፍላጻዎች የጐልማስነት ልጆች እንዲሁ ናቸው 5ከነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ብፁዕ ሰው ነው ጠላቶቻቸውን በአደባባይ በተናገሩ ጊዜ ርሱ አያፍ ርም