የመዓርግ መዝሙር።
1እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ እጅግ ደስተኛዎች ኾን፟ 2በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ 3እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን ደስም አለን 4አቤቱ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኳችንን መልስ 5በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ 6በኼዱ ጊዜ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዷቸውን ተሸክመው ደስ እያላ ቸው ይመጣሉ