የመዓርግ መዝሙር።
1በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘለዓለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው 2ተራራዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ኾኑ ከዛሬ ዠምሮ ለዘለዓለም እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው 3ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ የኃጥኣን በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም 4አቤቱ ለቸሮች ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ 5ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዐመፃን ከሚሠሩት ጋራ እግዚአብሔር ይወስዳቸዋል ሰላም በእስራኤል ላይ ይኹን