የዳዊት የመዓርግ መዝሙር።
1እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ባይኾን እስራኤል እንዲህ ይበል፦ 2እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ባይኾን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ 3ቍጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር 4በዚያን ጊዜ ውሃ ባሰጠመን ነበር በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር 5በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውሃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር 6ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ 7ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፦ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን 8ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው