የመዓርግ መዝሙር።
1ዐይኖቼ ወደ ተራራዎች አነሣኹ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ 2ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው 3እግርኽን ለመናወጥ አይሰጠውም የሚጠብቅኽም አይተኛም 4እንሆ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም 5እግዚአብሔር ይጠብቅኻል እግዚአብሔርም በቀኝ እጅኽ በኩል ይጋርድኻል 6ፀሓይ በቀን አያቃጥልኽም ጨረቃም በሌሊት 7እግዚአብሔር ከክፉ ዅሉ ይጠብቅኻል ነፍስኽንም ይጠብቃታል 8ከዛሬ ዠምሮ እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔር መውጣትኽና መግባትኽን ይጠብቃል