የመዓርግ መዝሙር።
1በተጨነቅኹ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኽኹ ሰማኝም 2ከዐመፀኛ ከንፈር ከሸንጋይም አንደበት አቤቱ ነፍሴን አድናት 3ስለሽንገላ አንደበት ምንም ይሰጡኻል ምንስ ይጨምሩልኻል 4እንደ በረሓ ዕንጨት ፍም የኀያላን ፍላጻዎች የተሳሉ ናቸው 5መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ በቄዳር ድንኳኖች ዐደርኹ 6ሰላምን ከሚጠሉ ጋራ ነፍሴ ብዙ ጊዜ ኖረች 7እኔ ሰላማዊ ነኝ በተናገርዃቸው ጊዜ ግን በከንቱ ተሰለፉብኝ