የዳዊት የመዓርግ መዝሙር።
1ወደእግዚአብሔር ቤት እንኺድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ 2ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ 3ኢየሩሳሌምስ ርስ በርሷ እንደ ተገጠገጠች ከተማ ተሠርታለች 4የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ ዘንድ ለእስራኤል ምስክር ሊኾኑ የእግዚአብሔር ነገዶች ወደዚያ ይወ ጣሉ 5ዙፋኖች በዚያ ለፍርድ ተቀምጠዋልና የዳዊት ቤት ዙፋኖች 6ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ አንተንም ለሚወዱ ልማት ይኹን 7በኀይልኽ ሰላም በጌጠኛ ቤትኽም ልማት ይኹን 8ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀራዎቼም በውስጥሽ ሰላም ይኹን አልኹ 9ስለአምላካችን ስለእግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግኹ