ሃሌ ሉያ።
1እስራኤል ከግብጽ የያዕቆብም ቤት ከእንግዳ ሕዝብ በወጣ ጊዜ 2ይሁዳ መቅደሱ እስራኤልም ግዛቱ ኾነ 3ባሕር አየች ሸሸችም ዮርዳኖስም ወደ ዃላው ተመለሰ 4ተራራዎች እንደ ኰርማዎች ኰረብታዎችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ 5አንቺ ባሕር የሸሸሽ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ዃላሽ የተመለሽ፟ ምን ኾናችዃል 6እናንተም ተራራዎች እንደ ኰርማዎች ኰረብታዎችስ እንደ ጠቦቶች ለምን ዘለላችኹ 7ከያዕቆብ አምላክ ፊት ከጌታ ፊት ምድር ተናወጠች 8ድንጋዩን ወደውሃ መቆሚያ ጭንጫውንም ወደውሃ ምንጭ ከለወጠ