ሃሌ ሉያ።
1ሃሌ ሉያ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ አመስግኑት የእግዚአብሔርንም ስም አመስግኑ 2ከዛሬ ዠምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይኹን 3ከፀሓይ መውጫ ዠምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን 4እግዚአብሔር በአሕዛብ ዅሉ ላይ ከፍተኛ ነው ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው 5እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው በላይ የሚኖር 6በሰማይና በምድር የተዋረዱትን የሚያይ 7-8 ከአለቃዎች ጋራ ከሕዝቡም አለቃዎች ጋራ ያኖረው ዘንድ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ ምስኪኑንም ከ ፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ 9መካኒቱን በቤት የሚያኖራት ደስ የተሠኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት ሃሌ ሉያ