ሃሌ ሉያ።
1ሃሌ ሉያ እግዚአብሔርን የሚፈራ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድ፟ ሰው ምስጉን ነው 2ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይኾናል የቅኖች ትውልድ ትባረካለች 3ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል 4ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ መሓሪና ይቅር ባይ ጻድቅም ነው 5ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም በፍርድም ነገሩን ይፈጽማል 6ለዘለዓለም አይናወጥም የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል 7ከክፉ ነገር አይፈራም በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው 8በጠላቶቹ ላይ እስኪያይ ድረስ ልቡ ጽኑ ነው አይፈራም 9በተነ ለችግረኛዎችም ሰጠ ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል ቀንዱ በክብር ከፍ ከፍ ይላል 10ኀጢአተኛም አይቶ ይቈጣል ጥርሱንም ያፋጫል ይቀልጣልም የኀጢአተኛዎችም ምኞት ትጠፋለች