ሃሌ ሉያ።
1ሃሌ ሉያ አቤቱ በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም በፍጹም ልቤ አመሰግንኻለኹ 2የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት ደስ በሚሠኙባት ዅሉ ዘንድ የተፈለገች ናት 3ሥራው ምስጋናና ግርማ ነው ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል 4ለተኣምራቱ መታሰቢያን አደረገ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው 5ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል 6የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ 7የእጆቹ ሥራ እውነትና ፍርድ ነው ትእዛዙም ዅሉ የታመነ ነው 8ለዘለዓለምም የጸና ነው በእውነትና በቅንም የተሠራ ነው 9መድኀኒትንም ለሕዝቡ ሰደደ ኪዳኑንም ለዘለዓለም አዘዘ ስሙ የተቀደሰና የተፈራ ነው 10የጥበብ መዠመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ለሚያደርጓትም ዅሉ ደኅና ማስተዋል አላቸው ምስጋና ውም ለዘለዓለም ይኖራል