የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ጌታዬን፦ጠላቶችኽን ለእግርኽ መቀመጫ እስካደርግልኽ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው 2እግዚአብሔር የኀይልን በትር ከጽዮን ይልክልኻል በጠላቶችኽም መካከል ግዛ 3ከአንተ ጋራ ቀድሞ በኀይልኽ ቀን በቅዱሳን ብርሃን ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድኹኽ 4እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነኽ ብሎ እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትም 5እግዚአብሔር በቀኝኽ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል 6በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል ሬሳዎችንም ያበዛል በሰፊ ምድር ላይ ራሶችን ይቀጠቅጣል 7በመንገድ ከፈሳሽ ውሃ ይጠጣል ስለዚህ ራስ ከፍ ከፍ ይላል