ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ 2ተቀኙለት ዘምሩለት ተኣምራቱንም ዅሉ ተናገሩ 3በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው 4እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችኹም ዅልጊዜ ፊቱን ፈልጉ 5-6 ባሪያዎቹ የአብርሃም ዘር ለርሱም የተመረጣችኹ የያዕቆብ ልጆች ሆይ የሠራትን ድንቅ ዐስቡ ተኣም ራቱን የአፉንም ፍርድ 7ርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው ፍርዱ በምድር ዅሉ ነው 8ቃል ኪዳኑን ለዘለዓለም እስከ ሺሕ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን ዐሰበ 9ለአብርሃም ያደረገውን ለይሥሐቅም የማለውን 10ለያዕቆብ ሥርዐት እንዲኾን ለእስራኤልም የዘለዓለም ኪዳን እንዲኾን አጸና 11እንዲህም አለ፦ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችኹን ገመድ እሰጣለኹ 12ይህም የኾነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች እጅግ ጥቂቶችና ስደተኛዎች ሲኾኑ ነው 13ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ከመንግሥታትም ወደ ሌላ ሕዝብ ዐለፉ 14-15 የቀባዃቸውን አትዳስሱ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ 16በምድር ላይ ራብን ጠራ የእኽልን ኀይል ዅሉ ሰበረ 17በፊታቸው ሰውን ላከ ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ 18እግሮቹም በእግር ብረት ደከሙ ርሱም በብረት ውስጥ ገባ 19ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው 20ንጉሥ ላከ ፈታውም የአሕዛብም አለቃ አስፈታው 21የቤቱ ጌታ የጥሪቱ ዅሉ ገዢ አደረገው 22አለቃዎቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኛዎች ያደርጋቸው ዘንድ 23እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ 24ሕዝቡንም እጅግ አበዛ ከጠላቶቻቸውም ይልቅ አበረታቸው 25ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ በባሪያዎቹም ላይ ይተ፟ነኰሉ ዘንድ ልባቸውን ለወጠ 26ባሪያውን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ 27የተኣምራቱን ነገር በላያቸው ድንቁንም በካም አገር አደረገ 28ጨለማን ላከ ጨለመባቸውም በቃሉም ዐመፁ 29ውሃቸውን ወደ ደም ለወጠ ዓሣዎቻቸውንም ገደለ 30ምድራቸው የንጉሦቻቸውም ቤቶች በጓጕንቸር ሞሉ 31ተናገረ የውሻ ዝንብ ትንኝም በዳርቻቸው መጡ 32ዝናባቸውን በረዶ አደረገው እሳትም በምድራቸው ተቃጠለች 33ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ የአገራቸውንም ዛፍ ዅሉ ሰበረ 34ተናገረ አንበጣም ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ መጣ 35የአገራቸውንም ለምለም ዅሉ በላ የምድራቸውንም ፍሬ በላ 36የአገራቸውንም በኵር ዅሉ የጕልበታቸውን መዠመሪያ ዅሉ መታ 37ከወርቅና ከብርም ጋራ አወጣቸው በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም 38ፈርተዋቸው ነበርና ግብጽ በመውጣታቸው ደስ አላት 39ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው እሳትንም በሌሊት ያበራላቸው ዘንድ ዘረጋ 40ለመኑ ድርጭትንም አመጣላቸው የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው 41አለቱን ሰነጠቀ ውሃውም ፈሰሰ ወንዞች በበረሓ ኼዱ 42ለባሪያው ለአብርሃም የነገረውን ቅዱስ ቃሉን ዐስቧልና 43ሕዝቡንም በደስታ የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ 44የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው የወገኖችንም ድካም ወረሱ 45ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ ሥርዐቱንም ይፈልጉ ዘንድ ሃሌ ሉያ