የጥበብ ውዳሴ
1አንተስ ጥበብን አስተምር፥ 2በተራሮች ጫፍ ላይ ናትና፥ 3በኀያላን በሮች ትጠብቃለች፥ 4እናንተ ሰዎች እናንተን እለምናለሁ፥ 5እናንተ የዋሆች፥ ጥበብን አስተውሉ፤ 6የተወደደች ነገርን እናገራለሁና ስሙ፤ 7አንደበቴ እውነትን ታስተምራለችና፥ 8የአፌ ቃላት ሁሉ እውነት ናቸው፤ 9በሚያውቁ ፊት ሁሉ የቀና ነው፥ 10ከብር ይልቅ ትምህርትን፥ 11ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍ ጥበብ ትበልጣለችና፥ 12እኔ ጥበብ ምክርን አሳደርሁ፥ 13እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ 14ምክርና ሥልጣን የእኔ ናቸው፤ 15ነገሥታት በእኔ ይነግሣሉ፥ 16ታላላቆች በእኔ ይከብራሉ። 17እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ 18ብልጥግናና ክብር 19ከወርቅና ከከበረ ዕንቍ ይልቅ እኔን መምረጥ ይሻላል፥ 20እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ 21ለሚወድዱኝ ሀብትን እከፍላቸው ዘንድ 22እግዚአብሔር ለሥራው የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፥ 23ምድርን ሳይፈጥር አስቀድሞ ከዓለም በፊት ሠራኝ፥ 24ቀላያትን ሳይፈጥር፥ 25ተራሮች ሳይመሠረቱ፥ 26እግዚአብሔር ከሰማይ በታች የሚታደርባቸውን 27ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥ 28ደመናትን በላይ ባጸና ጊዜ፥ 29ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ 30እኔ ከእርሱ ጋር እሠራ ነበር፤ 31ዓለምንም ፈጥሮ በፈጸመና ደስ ባለው ጊዜ፥ 32አሁንም ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ 33ጥበብን ስሙ፥ ጠቢባንም ሁኑ፥ 34የሚሰማኝ ሰው ብፁዕ ነው፥ 35መንገዶቼ የሕይወት መንገዶች ናቸውና። 36በእኔ ላይ በደልን የሚፈጽሙ ራሳቸውን ይበድላሉ፤