ከዝሙት ስለ መራቅ
1ልጄ ሆይ፥ ጥበቤን ተመልከት፤ 2መልካም ዐሳብን ትጠብቅ ዘንድ 3ከአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ 4ፍጻሜው ግን እንደ ሐሞት የመረረ ነው፥ 5እግሮችዋም ወደ ስንፍና ይወርዳሉ፥ 6በሕይወት መንገድም አትሄድም። 7አሁንም ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ 8መንገድህን ከእርስዋ አርቅ፥ 9ሕይወትህን ለሌላ እንዳትሰጥ፥ 10ባዕዳን በሀብትህ እንዳይጠግቡ፥ 11ሰውነትህ በደከመ ጊዜ፥ ኋላ ትጸጸታለህ፥ 12እንዲህም ትላለህ፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ! 13የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥ 14በማኅበርና በጉባኤ መካከል፥ 15ከማድጋህ ውኃ፥ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ። 16ከምንጮችህ ውኆች ወደ ሜዳ አይፍሰሱ። 17ለአንተ ብቻ ይሁኑ፥ 18የውኃ ምንጭህ ለአንተ ይሁንልህ፤ 19በዋሊያና በውርንጭላ ፍቅር፥ 20ልጄ ሆይ፥ ከሌላዪቱ ሴት ጋር አትኑር፤ 21የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ዐይኖች ፊት ነውና፥ 22ኀጢአት ሰውን ያጠምዳል፥ 23እርሱ ከሰነፎች ጋር ይሞታል፤