ከጥበብ የሚገኝ ጥቅም
1ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ 2መልካም ስጦታን እሰጣችኋለሁና፥ 3እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ 4ያስተምሩኝም ነበር፥ እንዲህም ይሉኝ ነበር፦ 5የአፌንም ቃል ቸል አትበል። 6አትተዋት፥ ትደግፍህማለች፤ 7ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ 8ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ 9ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥ 10ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፤ 11የጥበብን መንገዶች አስተምርሃለሁና፤ 12ብትሄድ ፍለጋህ አይጠፋም፤ 13ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤ 14በክፉዎች መንገድ አትሂድ፥ 15በተጓዙበትም ቦታ አትሂድ፤ 16ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ 17የኀጢአት መብልን ይበላሉ፥ 18የጻድቃን መንገዶች ግን እንደ ብርሃን ይበራሉ። 19የኃጥኣን መንገዶች ግን ጨለማ ናቸው። 20ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ፤ 21ምንጮችህ እንዳይደርቁ፥ 22ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥ 23ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥ 24ክፉ አፍን ከአንተ አርቅ፥ 25ዐይኖችህም አቅንተው ይዩ፥ 26ለእግርህ ቀና መሄጃ ሥራ፥ 27ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤