1መልካም ስም ከብዙ ባለ ጠግነት ይሻላል፥ 2ባለ ጠጋና ድሃ በአንድነት ተገናኙ፤ 3ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ 4እግዚአብሔርን መፍራት፥ 5እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ 6ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ 7ድሆች ባለጠጎችን ይገዛሉ፥ 8ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ 9ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል 10ነፍሰ ገዳይን ከጉባኤ አውጣ፥ ከእርሱም ጋር ክርክር ይወጣል፥ 11እግዚአብሔር የልብን የውሀት ይወድዳል። 12የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ 13ታካች ሰው በላኩት ጊዜ ያመካኛል፥ 14የዐመፀኛ አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ 15አለማወቅ የጐልማሳን ልብ ከፍ ከፍ አደረገች፤ 16ድሃን የሚቀማ ገንዘቡን ብዙ ያደርግለታል፥ 17ለመስማት ጆሮህን ወደ ጠቢባን ቃል አዘንብል፥ 18እነርሱን በልብህ ብትጠብቅ፥ 19ተስፋህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ 20ለዕውቀትና ለምክር ይሆኑህ ዘንድ ሦስት ነገሮችን እነሆ ጻፍሁልህ። 21በጎ ዕውቀትን ትሰማ ዘንድ፥ ለሚጠይቁህም የእውነት ቃልን ትመልስ ዘንድ 22ድሃን በግድ አትበለው፥ ድሃ ነውና 23እግዚአብሔር ፍርዱን ይፈርድለታልና። 24ከቍጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ 25መንገዱን እንዳትማር፥ 26የሰውን ፊት በማፈር ራስህን ለዋስትና አትስጥ። 27የምትከፍለው ባይኖርህ፥ 28አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን ድንበር አታፍርስ። 29ነገርን የሚረዳ፥ በሥራውም ብልህ የሆነ ሰው፥