1ብዙ ደስታ ከሞላበትና ከክርክር ጋር የዐመፃ ፍሪዳ ካለበት ቤት ይልቅ፥ 2ብልህ አገልጋይ አላዋቂዎች ጌቶችን ይገዛል፥ 3ብርና ወርቅ በከውር እንዲፈተን፥ 4ክፉ ሰው ከሕግ ውጭ የሆኑትን ሰዎች አንደበት ይሰማል፤ 5በድሃ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ያነሣሣዋል፥ 6የሽማግሌዎች አክሊል የልጅ ልጆች ናቸው፤ 7የታመነች ከንፈር ለሰነፍ፥ 8ትምህርት ገንዘብ ለሚያደርጓት የባለሟልነት ዋጋ ናት፥ 9በደሉን የሚሰውር ሰው ዕርቅን ይሻል፤ 10ትምክሕት የአስተዋይ ሰው ልቡናን ያሳዝነዋል፥ 11ክፉ ሰው ሁሉ ጠብን ያነሣሣል፤ 12ዐዋቂ ሰው በትካዜ ውስጥ ይወድቃል፥ 13በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ 14የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። 15ኃጥኡን ጻድቅ፥ ጻድቁንም ኃጥእ ብሎ መፍረድ 16ለአላዋቂ ሰው ገንዘብ ለምንድን ነው? 17ሁልጊዜ ወዳጅ ይኑርህ፥ 18አላዋቂ ሰው አጋና ይመታል፥ 19ክርክርን የሚወድድ በጠብ ደስ ይለዋል። 20ጠማማ ልብ ያለው መልካም ነገርን አያገኝም፥ 21የሰነፍ ልብ ገንዘብ ላደረጋት ኀዘን ናት፥ 22ደስ ያላት ልብ ፈውስን ታገኛለች፤ 23መማለጃን በዐመፃ በብብቱ የሚቀበል መንገዶቹን አያቀናም፥ 24የብልህ ሰው ፊት ዐዋቂ ነው፤ 25አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፥ 26ጻድቅን ሰው ማዋረድ መልካም አይደለም። 27ሻካራ ቃልን ከመናገር የሚከለክል ዐዋቂ ነው፥ 28አላዋቂ ጥበብን ቢጠይቅ ጥበብ ይሆነዋል፤