1እግዚአብሔርን መፍራት በጎ ዕውቀትና ጥበብ ነው። 2የትሑት ሰው ሥራ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው፥ 3ኃጥኣን ግን በክፉ ቀን ይጠፋሉ። 4በልቡ የታበየ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነው። 5የደግ መንገድ መጀመሪያ እውነት መሥራት ነው፥ 6እግዚአብሔርን የሚፈልግ ዕውቀትን ከጽድቅ ጋር ያገኛል፥ 7ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ። 8የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ከእውነት ጋር ነው። 9ኃጥእ ለክፉ ቀን ይጠበቃል። 10ጥበብ በንጉሥ አፍ አለ፥ 11የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ ሚዛን ውልብልቢት ነው፤ 12ክፉን የሚሠራም በንጉሥ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ 13የእውነት ከንፈር በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፥ 14የንጉሥ ቍጣ እንደ መልአከ ሞት ነው፤ 15የንጉሥ ልጅ እንደ ሕይወት ብርሃን ነው፥ 16ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። 17የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ 18ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ 19ከተሳዳቢዎች ጋር ምርኮን ከሚካፈል፥ 20በሥራ ዐዋቂ የሆነ መልካም ነገርን ያገኛል፤ 21ጠቢብን ሰዎች ዐዋቂ ይሉታል፥ 22በጎ ዐሳብ ገንዘብ ላደረጋት ሰው የሕይወት ምንጭ ናት፤ 23የጠቢብ ልብ ከአፉ ይታወቃል፥ 24ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ 25ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ 26ሰው በድካሙ ለራሱ ይደክማል፥ 27አላዋቂ ሰው ለራሱ ክፋትን ይምሳል፥ 28ጠማማ ሰው ክፋትን ይዘራል፥ 29ክፉ ሰው ወዳጆቹን ይዋሻል፥ 30በዐይኑ ትኩር ብሎ የሚመለከት፥ ጠማማ ዐሳብን ያስባል፤ 31መልካም ሽምግልና የክብር አክሊል ነው፥ 32ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ 33የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል።