1ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ 2የጠቢባን ምላስ መልካም ነገርን ታውቃለች፤ 3የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ 4ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ 5አላዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሥጽ ያቃልላል፤ 6በጻድቃን ቤቶች ብዙ ኀይል አለ፥ 7የጠቢባን ከንፈሮች በዕውቀት የታሰሩ ናቸው፤ 8የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ 9የክፉዎች መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ 10የቅኖች ትምህርት በሚያልፉ ሰዎች ትታወቃለች። 11ሲኦልና ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቁ ናቸው፤ 12አላዋቂ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ 13ልብ ደስ ሲለው ፊት ይበራል፤ 14ቀና ልብ ዕውቀትን ትፈልጋለች። 15የክፉዎች ዐይኖች ሁልጊዜ ክፋትን ይመለከታሉ፤ 16እግዚአብሔርን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ሀብት 17ጥል ካለበት የሰባ ፊሪዳ፥ 18ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ 19የሰነፎች መንገዶች እሾህ የተከሰከሰባቸው ናቸው፥ 20ብልህ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ 21የአላዋቂ ሰው መንገዶች ጠማሞች ናቸው፤ 22ማኅበርን የሚያከብሩ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ። 23ክፉ ሰው ግን ምክርን አይሰማትም፤ 24ሸሽቶ ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ፥ 25እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤ 26ዐመፃን ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ነው፤ 27መማለጃን የሚቀበል ራሱን ያጠፋል፤ 28የጻድቃን ልብ ታማኝነትን ይማራል፤ 29እግዚአብሔር ከኃጥኣን ፈጽሞ ይርቃል፤ 30መልካምን ነገር የሚያይ ዐይን ልብን ደስ ያሰኛል፥ 31የብልህን ተግሣጽ የሚሰማ ሰው 32ከተግሣጽ የሚከላከል ራሱን ይጠላል።